Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረህ ይባ​ር​ክ​ሃል፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም ብዙ ታበ​ድ​ራ​ለህ፤ አንተ ግን አት​በ​ደ​ርም፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ትገ​ዛ​ለህ፤ አን​ተን ግን አይ​ገ​ዙ​ህም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ስለሚባርክህ፣ አንተ ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ እንጂ ከማንም አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ እንጂ ማንም አንተን አይገዛህም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አምላክህ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ይባርክሃል፥ አንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ ከማንም ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ ማንም ግን አንተን አይገዛህም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ይባርክሃል፤ አንተ ለብዙ ሕዝቦች ገንዘብ ታበድራለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ከማንኛውም ሰው አትበደርም፤ አንተ በብዙ ሕዝቦች ላይ የበላይነት ይኖርሃል፤ በአንተ ላይ ግን ማንም የበላይ አይሆንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አምላክህም እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠህ ይባርክሃል፤ ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ፥ አንተ ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብንም ትገዛለህ፥ አንተን ግን አይገዙህም።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 15:6
14 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።


ድሆች ባለጠጎችን ይገዛሉ፥ አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው ያበድራሉ።


ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።


አቤቱ፥ አንተ አት​ጣ​ለኝ፤ አም​ላኬ፥ ከእኔ አት​ራቅ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እጅግ ኀያ​ላን ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ በወ​ን​ዝም ማዶ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብ​ር​ንና እጅ መን​ሻ​ንም ይቀ​በሉ ነበር።


ስለ​ዚህ በሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው ሰዎች እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ አስ​ጨ​ነ​ቋ​ቸ​ውም፤ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰ​ማ​ይም ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታዳ​ጊ​ዎ​ችን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ከሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ን​ሃ​ቸው።


እንደ አም​ላ​ካ​ችን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር።


ከወ​ንዙ ወዲህ ባሉት ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ ከወ​ን​ዙም ወዲህ ባለው ሀገር ሁሉ ላይ ከቲ​ላሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ባለው በሁሉ ወገን ሰላም ሆኖ​ለት ነበር።


ከኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ዳርቻ ድረስ ባሉ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነገሠ።


እርሱ ያበ​ድ​ር​ሃል፤ አንተ ግን አታ​በ​ድ​ረ​ውም፤ እርሱ ራስ ይሆ​ናል፤ አን​ተም ጅራት ትሆ​ና​ለህ።


አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ታደ​ር​ጋ​ትም ዘንድ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥


አሁ​ንም በፊ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖር ዘንድ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቤት ትባ​ርክ ዘንድ ጀም​ረ​ሃል፤ አን​ተም አቤቱ፥ ባር​ከ​ኸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቡሩክ ይሆ​ናል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios