ይህ ሕዝብ መሥዋዕት ለማቅረብ ኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ የሚወጣ ከሆነ፥ እንደገና ልቡን ወደ ጌታው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ሊያዞር ነው። ከዚያም እኔን ይገድለኛል፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሮብዓም ይመለሳል።”
ዘዳግም 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነገዶችህ መካከል በአንዱ፥ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ ብቻ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህን አቅርብ፤ እዚያም እኔ የማዝህን ሁሉ ጠብቅ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከነገዶችህ መካከል በአንዱ፣ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብቻ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህን አቅርብ፤ እዚያም እኔ የማዝዝህን ሁሉ ጠብቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሥዋዕትህን ሁሉ ማቅረብ የሚገባህ ከነገዶችህ መካከል የአንዱ ግዛት በሆነው ክፍል እና እግዚአብሔር በሚመርጠው በአንድ ስፍራ ብቻ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህንም ሆነ ሌላውንም እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ በዚያ ስፍራ ብቻ ትፈጽማለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብ፤ በዚያም ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሁሉ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብ፥ በዚያም የማዝዝህን ሁሉ አድርግ። |
ይህ ሕዝብ መሥዋዕት ለማቅረብ ኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ የሚወጣ ከሆነ፥ እንደገና ልቡን ወደ ጌታው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ሊያዞር ነው። ከዚያም እኔን ይገድለኛል፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሮብዓም ይመለሳል።”
የአሦር የጦር አዛዥ ንግግሩን በመቀጠል እንደገና እንዲህ አለ፦ “አምላክህ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ አድርገህ ታስባለህን? ይህማ እንዳይሆን፥ አንተ የእግዚአብሔርን የተቀደሱ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችን ደምስሰህ ‘የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ማምለክ የሚገባቸው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው በአንድ መሠዊያ ብቻ ነው’ ብለህ ወስነሃል።
በጌታ ማደሪያ ፊት ለፊት ለጌታ እንደ ቁርባን አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።
ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።
“ሆኖም ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ መጠን፥ በየትኛውም ከተማህ፥ እንስሳትህን ሚዳቋም ሆነ ድኩላ ዐርደህ የምትፈልገውን ያህል ሥጋ ብላ። በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነም ሆነ ያልሆነ ሰው ከዚሁ ሥጋ ሊበላ ይችላል።
አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፤ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል።
ምንጊዜም ጌታ እግዚአብሔርን ማክበር ትማር ዘንድ፥ የወይን ጠጅና የዘይትህን አሥራት፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ስፍራ፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ።
“በአንድ የነፍስ ግድያ ዓይነትና በሌላ፥ በአንድ ዓይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፥ ወይም በአንድ የክስ ዓይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጉዳይ ቢነሣ፥ ከአቅምህ በላይ የሆነ ጉዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፥ ተነሥተህ አምላክህ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ውጣ፤
በማደሪያው ፊት ለፊት ካለው ከአምላካችን ከጌታ መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በጌታ ላይ በማመፅ ጌታንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”