አሞጽ 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ በምድር ላይ ራብን የምልክበት ዘመን እየመጣ ነው፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እርሱም፦ የጌታን ቃላት ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፤ ይኸውም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ራብ እንጂ፣ እንጀራን የመራብ ወይም ውሃን የመጠማት አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ በምድር ላይ ራብን የማመጣበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ሰዎች የሚራቡትና የሚጠሙት የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ነው እንጂ ምግብና ውሃ በማጣት አይደለም፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም። |
ስለዚህ ለእናንተ ራእይ የሌለው ሌሊት ይሆንባችኋል፥ የማትጠነቁሉበት ጨለማ ይሆንባችኋል፤ ፀሐይ በነቢያት ላይ ትጠልቅባቸዋለች፥ ቀኑም ይጨልምባቸዋል።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “አስነሥተህ የምታውከኝ ለምንድነው?” አለው፤ ሳኦልም፥ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ፍልስጥኤማውያን እየወጉኝ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አልመለሰልኝም፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ” አለው።