ሐዋርያት ሥራ 6:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል፤’ ሲል ሰምተነዋልና፤” የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያጠፋና ከሙሴ የተቀበልነውን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ‘ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ቤተ መቅደስ ያፈርሳል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል’ ብሎ ሲናገር ሰምተነዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ቤተ መቅደስ ያፈርሰዋል፤ ሙሴም የሰጠንን ኦሪታችንን ይሽራል ሲል ሰምተነዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና” የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ። |
ኤርምያስም ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “የሰማችሁትን ቃላት ሁሉ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እንድናገር ጌታ ልኮኛል።
“ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል’ ብሎ ተናገረ።
አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እንዲነሱ እሰበስባቸዋለሁ፤ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማይቱም እኩሌታ ለምርኮ ይጋዛል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዋ አይፈናቃልም።
ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ በሥርዓትም እንዳይሄዱ ብለህ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁድ ሁሉ ሙሴን ይክዱ ዘንድ እንድታስተምር ስለ አንተ ነግረዋቸዋል።
ከሦስት ቀንም በኋላ ጳውሎስ የአይሁድን ታላላቆች ወደ እርሱ ጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው “ወንድሞች ሆይ! እኔ ሕዝቡን ወይም የአባቶችን ሥርዓት የሚቃወም አንዳች ሳላደርግ፥ ከኢየሩሳሌም እንደ ታሰርሁ በሮማውያን እጅ አሳልፈው ሰጡኝ።