Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 14:58 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

58 “ይህ፥ የሰው እጅ የሠራውን ቤተ መቅደስ አፍርሼ፥ በሦስት ቀን ሌላ የሰው እጅ ያልሠራውን እሠራለሁ ሲል ሰምተነዋል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

58 “ይህ፣ ‘የሰው እጅ የሠራውን ቤተ መቅደስ አፍርሼ፣ በሦስት ቀን ሌላ የሰው እጅ ያልሠራውን እሠራለሁ’ ሲል ሰምተነዋል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

58 “እኔ ይህን በሰው እጅ የተሠራውን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ ሌላ በሰው እጅ ያልተሠራ እሠራለሁ ብሎ ሲናገር ሰምተነዋል።”

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 14:58
11 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ክርስቶስ እንደ ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ ስለሚሆነው መልካም ነገር፥ በምትበልጠውና በምትሻለው፥ በእጆችም ባልተሠራች፥ እርሷም ከፍጡራን ባልሆነች ድንኳን፥


የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።


ኢየሱስም መልሶ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ፤” አላቸው።


ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ለመታየት ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ።


ነገር ግን ነቢዩ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?’ ይላል ጌታ፥ ‘ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን?’ እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።


በመንገድ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ ይሉት ነበር፤ “አይ፥ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራ አንተ ነህ፤


“ይህ ሰው ‘የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ልሠራው እችላለሁ’ ብሏል፤” አሉ።


አንዳንዶቹም ተነሥተው እንዲህ ሲሉ በሐሰት መሰከሩበት፤


ይህም ሆኖ፥ እንኳ ምስክርነታቸው አንድ አልሆነም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios