ሐዋርያት ሥራ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ካለ በኋላ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ካለ በኋላ እነርሱ እያዩት ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ደመናም ተቀብሎ ከዐይናቸው ሰወረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም እየነገራቸው ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ተቀበለችው፤ እነርሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከዐይናቸውም ተሰወረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። |
ጌታም ሙሴን፦ “ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙና ለዘለዓለም እንዲያምኑህ፥ እነሆ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለጌታ ነገረ።
ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
ደግሞም “የገሊላ ሰዎች ሆይ! ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል፤” አሉአቸው።
ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን የሆንነው፥ የቀረነውም ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።
እነዚህ ከሴቶች ጋር ያልረከሱ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበትም የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።