በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
2 ሳሙኤል 20:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገሩስ እንዲህ አይደለም፤ የኰረብታማው የኤፍሬሙ አገር ሰው፥ የቢክሪ ልጅ ሼባዕ እጁን በንጉሡ በዳዊት ላይ አንሥቶአል፤ እናንተ ይህን ሰው ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ከተማዪቱን ትቼ እሄዳለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፥ “የሰውየው ራስ ተቆርጦ በግንቡ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገሩስ እንዲህ አይደለም፤ የኰረብታማው የኤፍሬሙ አገር ሰው፣ የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ እጁን በንጉሡ በዳዊት ላይ አንሥቷል፤ እናንተ ይህን ሰው ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ከተማዪቱን ትቼ እሄዳለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፣ “የሰውየው ራስ ተቈርጦ በግንቡ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኛ ዕቅድ ይህ አይደለም፤ የተራራማው የኤፍሬም አገር ተወላጅ የሆነ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ የቢክሪ ልጅ በንጉሥ ዳዊት ላይ ዐመፅ አስነሥቶአል፤ ብቻ ይህ ሰው ይሰጠኝ እንጂ እኔ ከተማይቱን ለቅቄ እሄዳለሁ።” እርስዋም “ራሱን ቈርጠን በግንብ ላይ እንወረውርልሃለን” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሩ እንዲህ አይደለም፤ ከተራራማው ከኤፍሬም ሀገር የሚሆን የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄ የሚባል አንድ ሰው ግን በንጉሡ በዳዊት ላይ እጁን አነሣ፤ እርሱን ብቻውን ስጡኝ፤ እኔም ከከተማዪቱ እርቃለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፥ “እነሆ፥ ራሱ ከቅጥር ላይ ይጣልልሃል” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩ እንዲህ አይደለም፥ ከተራራማው ከኤፍሬም አገር የሚሆን የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ የሚባል አንድ ሰው ግን በንጉሡ በዳዊት ላይ እጁን አነሣ፥ እርሱን ብቻውን ስጡኝ፥ እኔም ከከተማይቱ እርቃለሁ አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፦ እነሆ፥ ራሱ ከቅጥር ላይ ይጣልልሃል አለችው። |
በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
ስለዚህ የእስራኤል ሰው ሁሉ ዳዊትን ከድቶ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ተከተለ። የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንሥቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው ሳይለዩ አብረውት ሄዱ።
የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና ስሙም ከሦስቱ ኀያላን ጋር የሚጠራ ነበረ።
በሰሎሞን ላይ ያመፀው ሌላው ሰው በኤፍሬም ጸሬዳ ተብላ የምትጠራው ክፍለ ሀገር ተወላጅ የሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነው፤ እርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች አንዱ ነበር፤ እናቱም ጽሩዓ ተብላ የምትጠራ ባሏ የሞተባት ሴት ነበረች።
የኢዩ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው የሰማርያ መሪዎች ሰባውንም የአክዓብ ተወላጆች በሙሉ ገደሉ፤ ራሶቻቸውንም በመቁረጥ በቅርጫት ሞልተው በኢይዝራኤል ወደነበረው ወደ ኢዩ ላኩለት።
ግያዝም “መምጣትስ በደኅና ነው የመጣሁት፤ ነገር ግን ጌታዬ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖሩ ሁለት የነቢያት ጉባኤ አባላት ድንገት በእንግድነት ስለ መጡበት፥ ሦስት ሺህ ብርና ሁለት መቀየሪያ ልብስ እንድትሰጣቸው እነግርህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል” ሲል መለሰለት።
ጌዴዎንም በኤፍሬም ኰረብታማ አገር ለሚኖሩት ሁሉ፥ “በምድያማውያን ላይ ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስ ወንዝ ቀድማችሁ ያዙ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጡ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስን ወንዝ ያዙ።