መሳፍንት 7:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ጌዴዎንም በኤፍሬም ኰረብታማ አገር ለሚኖሩት ሁሉ፥ “በምድያማውያን ላይ ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስ ወንዝ ቀድማችሁ ያዙ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጡ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስን ወንዝ ያዙ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ጌዴዎንም መልእክተኞቹን ልኮ፣ በኤፍሬም ኰረብታማ አገር ለሚኖሩት ሁሉ፣ “በምድያማውያን ላይ ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስ ወንዝ ቀድማችሁ ያዙ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጡ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስን ወንዝ ያዙ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ጌዴዎንም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳሉት ሁሉ መልእክተኞች ልኮ “ወርዳችሁ በምድያማውያን ላይ ዝመቱ፤ ምድያማውያን ተሻግረው እንዳያመልጡ የዮርዳኖስን ወንዝና ወደ እርሱ የሚገቡትንም መጋቢ ወንዞች እስከ ቤትባራ ድረስ በር በሩን ዘግታችሁ በተጠናከረ ሁኔታ ጠብቁ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች በአንድነት ተጠራርተው የዮርዳኖስን ወንዝና ወደዚያ የሚገቡትን መጋቢ ወንዞች እስከ ቤተባራ ድረስ ዘግተው ያዙ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ጌዴዎንም፥ “ምድያማውያንን ለመግጠም ውረዱ፥ እስከ ቤትባራም ድረስ ያለውን ውኃ፥ ዮርዳኖስንም፥ ያዙባቸው” ብሎ መልእክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ተራራማ ሀገር ሁሉ ላከ። የኤፍሬምም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው እስከ ቤትባራ ድረስ ውኃውን፥ ዮርዳኖስንም ቀድመው ያዙ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ጌዴዎንም፦ ምድያምን ለመገናኘት ውረዱ፥ እስከ ቤትባራም ድረስ ያለውን ውኃ፥ ዮርዳኖስን፥ ያዙባቸው ብሎ መልክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ተራራማ አገር ሁሉ ሰደደ። የኤፍሬም ሰዎችም ሁሉ ተሰብስበው እስከ ቤትባራ ድረስ ውኃውን፥ ዮርዳኖስን፥ ያዙ። Ver Capítulo |