አማሳይንም፥ ‘አንተስ የዐጥንቴ ፍላጭ፥ የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ እስከ ሕይወትህ ፍጻሜ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባላደርግህ፥ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፥ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ’ ብላችሁ ንገሩት።”
2 ሳሙኤል 19:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሰዎች፥ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቆጣ ነገር ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች፣ “እኛ እኮ ከንጉሡ ዐሥር እጅ ድርሻ አለን፤ ከዚህም በተጨማሪ በዳዊት ላይ ከእናንተ ይልቅ እኛ የበለጠ መብት አለን፤ ታዲያ እኛን የናቃችሁን ስለ ምንድን ነው? ንጉሣችን እንዲመለስ በመጀመሪያ የጠየቅነው እኛ አይደለንምን?” አሉ። ነገር ግን የይሁዳ ሰዎች የሰጡት መልስ የእስራኤል ሰዎች ከሰጡት መልስ ይልቅ እጅግ የከረረ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም “እርሱ የእናንተ ወገን ቢሆንም እንኳ እናንተ ከምትፈልጉት ይበልጥ እኛ እንፈልገዋለን፤ ከመንግሥቱ ዐሥሩ እጅ የሚገባው ለእኛው ነው፤ እናንተ እኛን የምትንቁት ስለምንድን ነው? ንጉሡን ስለ መመለስ በመጀመሪያ ጥያቄ ያቀረብነው እኛ መሆናችንን ልትዘነጉ አይገባም!” አሉአቸው። ነገር ግን ከእስራኤል ሰዎች ይልቅ የይሁዳ ሰዎች ዳዊትን የራሳቸው ለማድረግ በብርቱ ተከራከሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች መልሰው፥ “በንጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእናንተም እኛ እንቀድማለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳዊትም ከእናንተ እኛ እንቀርባለን፤ ስለምን ናቃችሁን? ንጉሡንስ እንመልሰው ዘንድ ከእናንተ የእኛ ቃል አይቀድምምን?” አሏቸው። የይሁዳም ሰዎች ቃል ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነከረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች መልሰው፦ በንጉሡ ዘንድ ለእኛ አሥር ክፍል አለን፥ በዳዊትም ዘንድ ደግሞ ከእናንተ ይልቅ መብት አለን፥ ስለ ምን ናቃችሁን? ስለ ምንስ ንጉሣችንን ለመመለስ ቀድሞ ምክር አልጠየቃችሁንም? አሉ። የይሁዳም ሰዎች ቃል ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነከረ። |
አማሳይንም፥ ‘አንተስ የዐጥንቴ ፍላጭ፥ የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ እስከ ሕይወትህ ፍጻሜ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባላደርግህ፥ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፥ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ’ ብላችሁ ንገሩት።”
ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በበሩ አጠገብ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም፥ “እነሆ ንጉሡ በበሩ አጠገብ ተቀምጦአል” ተብሎ በተነገረ ጊዜ ሕዝቡ በሙሉ ወደ ንጉሡ መጣ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየቤታቸው ሸሽተው ነበር።
በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
ዳዊትም አቢሳን፥ “ከአቤሴሎም ይልቅ አሁን የቢክሪ ልጅ ሼባዕ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስብን ስለሆነ የጌታህን አገልጋዮች ይዘህ አሳደው፤ ያለዚያ የተመሸገ ከተማ አግኝቶ ያመልጠናል” አለው።
ሕዝቡ፥ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ “ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ከዳዊት ጋር ምን ርስት አለን፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየድኳንኖችህ ሂድ! ዳዊት ሆይ የራስህን ቤት ጠብቅ!” ብለው መለሱለት። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ።
ከራስ ወዳድነት ወይም ከትምክሕት የተነሣ አንድም ነገር አታድርጉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በትሕትና ባልንጀራውን ከራሱ ይልቅ እንደሚሻል አድርጎ ይቁጠር፤
በዚያን ጊዜ የኤፍሬም ሰዎች፥ “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ ለምን አልጠራኸንም? ለምንስ እንዲህ ያለ ነገር አደረግህ?” በማለት ጌዴዎንን እጅግ ነቀፉት።