2 ጴጥሮስ 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልእክቶቹም ሁሉ እንዳደረገው ስለዚህ ነገር ተናግሯል። በመልእክቶቹ ውስጥ አንዳንድ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ፤ ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ ሁሉ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፏል፤ በመልእክቶቹም ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ፣ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ስለዚህ ጉዳይ በመልእክቶቹ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ጽፎአል፤ በመልእክቶቹ ውስጥ አንዳንድ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ወላዋዮች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህንም ነገሮች ያጣምማሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት ለጥፋታቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። |
ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆንበታልና ‘የጌታ ሸክም’ ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ፤ የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የሕያው እግዚአብሔርን ቃላት ለውጣችኋልና።
ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይኖራሉ፤ እነርሱም ጥፋትን የሚያስከትሉ ትምህርቶች አስርገው በማስገባት የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፥ በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋትን ያመጣሉ።
ከዚህ በፊት በቅዱሳን ነቢያት የተነገረውን ቃል፥ እንዲሁም በሐዋርያዎቻችሁም አማካይነት ያገኛችኋትን የጌታችንንና የመድኃኒታችንን ትእዛዝ እንድታስቡ ይገባል።
አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።