La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 9:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋዮቹም በሠረገላ አድርገው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋራ በመቃብሩ ቀበሩት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብላ​ቴ​ኖ​ቹም በሰ​ረ​ገ​ላው ጭነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በመ​ቃ​ብሩ ቀበ​ሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያዎቹም በሠረገላው ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊትም ከተማ በመቃብሩ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 9:28
9 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ሞተ፤ የእርሱ ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌምም ተቀበረ።


ባርያዎቹም ተነሥተው ዐመፁበት፥ ወደ ሲላ በሚወርደውም መንገድ በሚሎ ቤት ገደሉት።


በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ያገለግሉ የነበሩትንም አሕዛብ ካህናትን ገደለ፤ በመሠዊያዎቹም ላይ አጥንት አቃጠለባቸው። ይህን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።


ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የይሁዳም ሰዎችም የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መረጡ፤ ቀብተውም አነገሡት።


ኢዮራም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ ውስጥ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አካዝያስ ነገሠ።


አካዝያስንም ፈልገው፥ በሰማርያም ተሸሽጎ ሳለ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት እንዲህም ብለው ቀበሩት፦ “በፍጹም ልብ ጌታን የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው።” ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥቱን ለመግዛት የሚችል አልነበረም።


በፈረስም ጭነው አመጡት፥ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት።


አገልጋዮቹም ከሠረገላው አውርደው ለእርሱ በነበረው በሁለተኛው ሠረገላ ውስጥ አስቀመጡት፥ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጡት፤ እርሱም ሞተ፥ በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌምም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱ።