2 ነገሥት 25:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ ባቢሎናውያን ከተማዪቱን እንደ ከበቧት ቢሆንም የከተማዪቱ ቅጥር ተጣሰ፤ ሰራዊቱም ሁሉ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ባሉት በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በዓረባ በር ዐልፎ በሌሊት ሸሸ፤ ሽሽቱም ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተማዪቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ በሁለት ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ሸሹ፤ ከለዳውያንም በከተማዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ምድረ በዳ በሚወስደውም መንገድ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተማይቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ በሁለት ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ሸሹ፤ ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓረባም መንገድ ሄዱ። |
ንጉሥ ሕዝቅያስም ራሱን ለሥራ ጽኑ አደረገ፥ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፥ በላዩም ግንብ ሠራበት፥ ከእርሱም በስተ ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ በዳዊትም ከተማ ያለችውን ሚሎን አጠነከረ፤ ብዙም የጦር መሣሪያና ጋሻ ሠራ።
የሚጽጳም አውራጃ ገዢ የኮልሖዜ ልጅ ሻሉን “የምንጭ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ ከደነውም፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ፤ በንጉሡ አትክልት ቦታ አጠገብ ያለውን የሼላሕን መዋኛ ቅጥር ከዳዊት ከተማ ወደ ታች እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ ሠራ።
በአሮጌው ኩሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፥ ቀድሞ አቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።
የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፥ ፊት ለፊትም ያነጋግረዋል፥ ዓይኑም ዓይኑን ያያል እንጂ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፤
አንተም በእርግጥ ትያዛለህ ለእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም፤ ዓይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፥ እርሱም ከአንተ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገራል፥ ወደ ባቢሎንም ትሄዳለህ።’
ከፈረሰኛና ከቀስተኛ ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ትሸሻለች፤ ጥቅጥቅ ወዳለ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፤ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው ነፍሱንም ለሚሻው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፥ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚሽዋት እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”
ጋሜል። ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች፥ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፥ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት።
በመካከላቸውም ያለው ልዑል በትከሻው ላይ ተሸክሞ በጨለማ ይወጣል፥ በዚያም ሊወጡ ግንቡን ይቦረቡራሉ፥ በዓይኑም ምድሪቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።
እንዲህም ሆነ፥ በተማረክን በዓሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተማይቱ ተመታች አለኝ።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።
የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም፥ የአምስተኛው፥ የሰባተኛው፥ የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ፥ የሐሤትም በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ!
“ጌታ በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ በሚደርስብህም ነገር ለምድር መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ።