የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
2 ነገሥት 19:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ። |
የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’”
የሦስት ዓመት ራብ፥ ወይም ሦስት ወር የጠላቶችህ ሰይፍ እንዲያገኝህ ከጠላቶችህም ፊት እንድትሰደድ፥ ወይም ሦስት ቀን የጌታ ሰይፍ ቸነፈርም በምድር ላይ እንዲሆን፥ የጌታም መልአክ በእስራኤል ምድር ሁሉ ጥፋትን እንዲያመጣ ምረጥ፤’ ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አሁን ወስን።”
ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የጌታ መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
የይሁዳም ሰዎች በምድረ በዳ ወዳለው የመጠበቅያ ግንብ በመጡ ጊዜ ሕዝቡን አዩ፤ እነሆም፥ በምድሩ ሁሉ ሬሳ ሞልቶ ነበር፥ ያመለጠም ሰው አልነበረም።
ጌታ ግብጽን ሊመታ ያልፋል፤ ደሙንም በጉበኖቹና በሁለቱ መቃኖች ላይ ያያል፥ ጌታም በበሩ ያልፋል፥ አጥፊውም ሊመታችሁ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይፈቅድም።
ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፤ እነርሱንም በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በጌታ አድናቸዋለሁ።”