ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ፤ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።
2 ነገሥት 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የበዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደለው። ዮዳሄ ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የአገሩ ሕዝብ ሁሉ ሄደው የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደለው። ዮዳሄ ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበሩት፤ መሠዊያዎቹንም አፈረሱ፤ ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም ለእግዚአብሔር ቤት ጠባቂዎችን ሾመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን አደቀቁ፤ የበኣልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑም ለእግዚአብሔር ቤት አስተዳዳሪዎችን ሾመ። |
ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ፤ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።
ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ በዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤
ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥
በዚህም ዓይነት ጣዖት አምላኪዎቹ የተቀደሰ ነው ብለው የሚያምኑበትን የድንጋይ ዐምድና ቤተ መቅደሱን አፈራረሱ፤ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ አደረጉት፤ ዛሬም በዚሁ ዓይነት ይገኛል።
የአሕዛብን የማምለኪያ ስፍራዎችን ደመሰሰ፤ የድንጋይ ዐምዶችን ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የተቀረጹትን ምስሎች ሁሉ አንኮታክቶ ጣለ፤ ሙሴ ከነሐስ ሠርቶት የነበረውን ኔሑሽታን ተብሎ የሚጠራውን የእባብ ምስል ሰባብሮ አደቀቀ፤ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ግን እስራኤላውያን ለእርሱ ዕጣን ያጥኑለት ነበር።
ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤
ንጉሥ ኢዮስያስ የድንጋይ ዐምዶችን ሁሉ ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስሎች አንኮታክቶ ጣለ፤ እነርሱ ቆመውበት የነበረውንም ስፍራ የሙታን አጥንት ሞላበት።
በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ያገለግሉ የነበሩትንም አሕዛብ ካህናትን ገደለ፤ በመሠዊያዎቹም ላይ አጥንት አቃጠለባቸው። ይህን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
ወደ ይሁዳም ወጡ፥ ወረርዋትም፥ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም ሴቶች ልጆቹንም ማረኩ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አላስቀሩለትም።
የበኣሊምንም መሠዊያዎች በእርሱ ፊት አፈረሱ፤ በእነርሱም ላይ የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎቹን የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የተቀረፁትንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች ሰባበረ፥ አደቀቃቸውም፥ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብርም ላይ በተናቸው።
መሠዊያዎቹንም አፈረሰ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረፁትን ምስሎች አደቀቀ፥ በእስራኤልም አገር ሁሉ የዕጣን መሠዊያዎቹን ሁሉ ቈራረጠ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው አሕዛብ በረጅሙ ተራሮች፥ በኰረብቶችና በእያንዳንዱ ዛፍ ሥር አማልክታቸውን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።
መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፤ የማምለኪያ አምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የ ‘አሼራ’ ምስል ዐምዶቻቸውን በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን ጣዖቶች ቆራርጣችሁ ጣሉ፤ ስማቸውንም ከእነዚያ ስፍራዎች ላይ አጥፉ።”
ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በጌታ ላይ ሊያስታችሁ ተናግሮአልና፥ አምላካችሁ ጌታ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፥ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።”
“የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥