አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”
2 ነገሥት 10:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን የኃጢአት መንገድ ከመከተል አልተገታም፤ ኢዩ ራሱ ቀደም ሲል የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤልና በዳን ላቆማቸው የወርቅ ጥጃ ምስሎች መስገዱ አልቀረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ኢዩ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም፣ በቤቴልና በዳን የወርቅ ጥጆች እንዲያመልኩ እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልራቀም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን የኃጢአት መንገድ ከመከተል አልተገታም፤ ኢዩ ራሱ ቀደም ሲል የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤልና በዳን ላቆማቸው የወርቅ ጥጃ ምስሎች መስገዱ አልቀረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት ኢዩ አልራቀም፥ በቤቴልና በዳን የነበሩትን የወርቅ እንቦሶችንም፥ አላስወገደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት፥ በቤቴልና በዳን ከነበሩት ከወርቁ እምቦሶች፥ ኢዩ አልራቀም። |
አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”
ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራቸውን የኢዮርብዓምን ክፉ አርአያነት ተከተለ።
እርሱም ከእርሱ በፊት እንደነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እስራኤልንም ወደ ኃጢአት መራ፤ ከክፉ ሥራውም ከቶ አልተገታም።
ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።
እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱም እግዚአብሔርን አሳዘነ።
እርሱም ከእርሱ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት ሁሉ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እንዲሁም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት ተከተለ፤
ከእጃቸው ተቀብሎ በቅርጽ መሥሪያ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃ አደረገው፤ እርሱም፦ “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” አላቸው።
ከግብጽ ጀምሮ የነበረውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በወጣትነትዋ ጊዜ ወንዶች ከእርሷ ጋር ተኝተው ነበርና፥ የድንግልናዋንም የጡቶቿ ጫፎች ዳብሰው ነበርና፥ ፍትወታቸውንም አፍስሰውባት ነበርና።
አሁንም ኃጢአትን እጅግ አብዝተው ይሠራሉ፤ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፤ ሁሉም የሞያተኞች ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም የሚሠዉ ሰዎች፦ “እምቦሳውን ይሳሙ” ይላሉ።