እንዲህም በሉ፦ “የመዳናችን አምላክ ሆይ! አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እንድናመሰግን፥ በምስጋናህም እንድንከብር፥ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበኸን ታደገን።
2 ቆሮንቶስ 9:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቃላት ሊገለጥ ስለማይቻል ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰው ቃል ሊነገር ስለማይቻለው ስጦታው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለማትመረመርና ባላሰቡአት ጊዜ ስለምትመጣው ጸጋው እግዚአብሔር ይመስገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። |
እንዲህም በሉ፦ “የመዳናችን አምላክ ሆይ! አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እንድናመሰግን፥ በምስጋናህም እንድንከብር፥ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበኸን ታደገን።
እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።
ለመንግሥቱ ስፋት፤ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፤ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዘለዓለም አባት ቅናት ይህን ያደርጋል።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ከሞቱ፥ ይልቁንም የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ያለው ስጦታ ለብዙዎች እንዴት ይበዛ።