ሰሎሞን ከዚሁ ሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፥ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያም በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አያውቅም።
2 ዜና መዋዕል 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለጌታ ቤትና ለንጉሡ ቤት እርከኖችን፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና ሠራ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም የሰንደሉን ዕንጨት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ለቤተ መንግሥቱ ደረጃ መሥሪያ እንደዚሁም ለመዘምራኑ የመሰንቆና የበገና መሥሪያ አደረገው፤ ይህን የመሰለ ነገር በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞንም የሰንደሉን እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን ደረጃዎች እንዲሁም የመዘምራኑን መሰንቆና በገና አሠራበት፤ እነዚህን የዜማ መሣሪያዎች የመሰለ ከዚያ በፊት በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር። |
ሰሎሞን ከዚሁ ሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፥ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያም በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አያውቅም።
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
ደግሞም ባርያዎችህ ከሊባኖስ እንጨት መቁረጥ እንደሚያውቁ እኔ አውቃለሁና ከሊባኖስ የዝግባና የጥድ የሰንደልም እንጨት ላክልኝ፤ እነሆ፥ ባርያዎቼ ከባርያዎችህ ጋር በመሆን
የሳባም ንግሥት ወደ ንጉሡ ካመጣችው የሚበልጥ፥ ንጉሡ ሰሎሞን የፈለገችውን ሁሉ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ሰጣት፤ እርሷም ተመልሳ ከባርያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች።
መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።