2 ዜና መዋዕል 36:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የባቢሎናውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የባቢሎን ንጉሥ በእነርሱ ላይ አደጋ እንዲጥል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ንጉሡም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን እንኳ ሳይቀር፥ በይሁዳ የሚገኙትን ወጣቶች ወንዶችን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር አሳልፎ ስለ ሰጣቸውም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ማንንም ሳይለይ፥ ሁሉንም ያለ ምሕረት አጠፋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጐልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ለንጉሣቸው ለሴዴቅያስም አልራራለትም፤ ደናግሉንም አልማረም፤ ሽማግሌዎቻቸውንም ወሰዳቸው፤ ሁሉንም እግዚአብሔር በእጁ አሳልፎ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን፥ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎችዋ ላይ አመጣለሁ።
ነገር ግን አባቶቻችን የሰማያትን አምላክ ስላስቆጡት በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፥ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ።
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ በታላቅ በደል ነበርን፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስለ ኃጢአታችን እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናቶቻችን ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለእፍረት በምድር ነገሥታት እጅ ተሰጠን።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።
ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፥ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም፥ ስለ እነርሱም ማንም ገላውን አይነጭም ራሱንም አይላጭም፤
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፥ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፥ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፥ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፥ ጉልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል በላከበት ጊዜ ነው፦
ከዚህ በኋላ፥ ይላል ጌታ፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህችም ከተማ የቀሩትን፥ አገልጋዮቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።’
ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ ለከለዳውያን እጅና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ይይዛታል።
ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፥ እንዲሁ ለእነርሱ የተናገርሁትን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።
አንተም የሰው ልጅ ሆይ፦ ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፤ ቀናቸው በደረሰ፥ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ በደረሰ፥ በተገደሉት ኃጢአተኞች
ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።