Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 30:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ፈጽመህ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬ እነግርሃለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ እንድትወርሳትም በምትገባባት ምድር ረጅም ዘመን አትኖርም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንደምትደመሰስ እነሆ፥ ዛሬ አስጠነቅቅሃለሁ። ዮርዳኖስን ተሻግረህ በምትወርሳት ምድር ለረጅም ዘመን አትኖርም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ረህ ትወ​ር​ሳት ዘንድ በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ዘመ​ንህ አይ​ረ​ዝ​ምም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ፈጽማችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ዘመናችሁን አታስረዝሙም።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 30:18
10 Referencias Cruzadas  

ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ለምስክርነት እጠራለሁ፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረጅም ዘመን አትኖሩባትም።


እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ ዐውቃለሁና። በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፥ እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ስለምታስቆጡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።”


እርሱን ከመከተል ብትመለሱ እርሱ ዳግመኛ ሕዝቡን በምድረ በዳ ይተዋል፤ ይህንንም ሕዝብ ሁሉ ታጠፋላችሁ።”


ልብህ ግን ርቆ አንተም ባትሰማ፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድላቸውና ብታመልካቸው ግን፥


“ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ ማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ ከረከሳችሁ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በጌታ በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከሠራችሁ፥


በዚያች ቀን እቀጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፥ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።


ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገ ባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios