ከዚህ በኋላ ጸሐፊው ሳፋን ከንጉሡ የተላከውን ትእዛዝ ለሒልቂያ ሰጠ፤ ሒልቂያም “የሕጉን መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘሁ” ብሎ ለሳፋን ሰጠው፤ ሳፋንም ተቀብሎ አነበበው፤
2 ዜና መዋዕል 34:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኬልቅያስም ጸሐፊውን ሳፋንን፦ “የሕጉን መጽሐፍ በጌታ ቤት አግኝቼአለሁ” ብሎ ተናገረው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኬልቅያስም ጸሓፊውን ሳፋንን፣ “የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አገኘሁት” አለው፤ ከዚያም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ጸሐፊውን ሳፋንን “የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ በዚህ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አግኝቻለሁ” በማለት መጽሐፉን ሰጠው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኬልቅያስም ጸሓፊውን ሳፋንን፥ “የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤት አግኝቼአለሁ” ብሎ ነገረው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኬልቅያስም ጸሐፊውን ሳፋንን “የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤት አግኝቼአለሁ” ብሎ ተናገረው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው። |
ከዚህ በኋላ ጸሐፊው ሳፋን ከንጉሡ የተላከውን ትእዛዝ ለሒልቂያ ሰጠ፤ ሒልቂያም “የሕጉን መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘሁ” ብሎ ለሳፋን ሰጠው፤ ሳፋንም ተቀብሎ አነበበው፤
ንጉሡም፥ የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩና ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም፥ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀመሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ጌታ ቤት ወጡ፤ በጌታም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ እየሰሙት አነበበ።
ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ ጌታ ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሐፊው ለዕዝራ ነገሩት።