Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 34:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ወደ ጌታም ቤት የቀረበውን ገንዘብ ባመጡ ጊዜ ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ እጅ የተሰጠውን የጌታን የሕግ መጽሐፍ አገኘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የገባውን ገንዘብ በሚያወጡበት ጊዜ፣ ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የቀረበውን ገንዘብ ከግምጃ ቤት ያወጡ በነበሩበት ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ሒልቂያ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ገን​ዘብ ባመጡ ጊዜ ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በሙሴ እጅ የተ​ሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ አገኘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ወደ እግዚአብሔርም ቤት የቀረበውን ገንዘብ ባመጡ ጊዜ ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ እጅ የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 34:14
19 Referencias Cruzadas  

ሁሉንም ነገር እንደ ጌታ ሕግ ከፈጸሙ በኋላ፥ ወደ ገሊላ ወደ ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ።


“እናንተስ፦ ‘ጥበበኞች ነን የጌታንም ሕግ ከእኛ ጋር ነው’ እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ በውኑ የጸሐፊዎች ሐሰተኛ ብዕር ሐሰት አድርጎታል።


ዓመጸኛ ወገንና የጌታን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና፤


ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፤ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፤ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል።


ነገር ግን በጌታ ሕግ ደስ የሚለው፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ።


ዕዝራም የጌታን ሕግ ሊፈልግና ሊያደርግው፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ሊያስተምር ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።


የቀረውም የኢዮስያስ ነገር፥ በጌታም ሕግ እንደ ተጻፈ ያደረገው ቸርነት፥


ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኬልቅያስ መጡ፤ ሌዋውያኑም የደጆቹም ጠባቂዎች ከምናሴና ከኤፍሬም ከቀረውም ከእስራኤል ሁሉ፥ ከይሁዳና ከብንያም ሁሉ በኢየሩሳሌምም ከሚኖሩት የሰበሰቡትን፥ ወደ ጌታ ቤት ያመጡትን ገንዘብ ሰጡት።


የጌታንም ሕግ በጽኑ እንዲያገለግሉ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚገባቸውን ድርሻ እንዲሰጡአቸው በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሕዝብ አዘዘ።


እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜ፥ እርሱም በበረታ ጊዜ፥ እርሱና እስራኤል ሁሉ የጌታን ሕግ ተዉ።


የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአንደበትህ አይለይ፥ ነገር ግን በእርሱ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ እንድትጠብቅና እንድታደርገው በቀንም በሌሊትም አሰላስለው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቃናልሃል ይከናወንልሃልም።


ጌታም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰጣቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።


ጌታም በሙሴ አንደበት የነገራቸውን ሥርዓት ሁሉ ለእስራኤል ልጆች እንድታስተምሩ ነው።”


አሮንና ልጆቹም ጌታ በሙሴ አንደበት ያዘዘውን ቃላት ሁሉ አደረጉ።


ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለ ሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤


ኬልቅያስም ጸሐፊውን ሳፋንን፦ “የሕጉን መጽሐፍ በጌታ ቤት አግኝቼአለሁ” ብሎ ተናገረው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios