2 ዜና መዋዕል 33:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም፦ “ስሜ በኢየሩሳሌም ለዘለዓለም ይኖራል” ባለው በጌታ ቤት መሠዊያዎችን ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ “ስሜ ለዘላለም በኢየሩሳሌም ይኖራል” ባለበት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠዊያዎችን ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለዘለዓለም ስሙ ይጠራበታል ባለው ስፍራ፥ ማለትም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን ተከለ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፥ “ስሜ በኢየሩሳሌም ለዘለዓለም ይኖራል” ባለው በእግዚአብሔር ቤት የጣዖት መሠዊያዎችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም “ስሜ በኢየሩሳሌም ለዘላለም ይኖራል” ባለው በእግዚአብሔር ቤት መሠዊያዎችን ሠራ። |
“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።
እንግዶችንም አማልክትና ጣዖቱንም ከጌታ ቤት አራቀ፥ የጌታም ቤት ባለበት ተራራ ላይና በኢየሩሳሌም የሠራቸውን መሠዊያዎች ሁሉ ወስዶ ከከተማይቱ በስተ ውጭ ጣላቸው።
ጌታ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን፦ “በዚህ ቤት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤” ባለበት በጌታ ቤት የሠራውን ጣዖት የቀረጸውን ምስል አቆመ።
እነርሱም የይሁዳ ነገሥታት ላፈረሱት ቤት ሰረገሎች እንዲሠሩ፥ ለማጋጠሚያም እንጨት የተጠረበውንም ድንጋይ እንዲገዙ ለአናጢዎችና ለጠራቢዎች ሰጡ።
‘ህዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤት በዚያ እንዲሠራልኝ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥሁም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ እንዲሆን ማንንም አልመረጥሁም፤
ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።