Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 32:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በሰውም እጅ በተሠሩ በምድር አሕዛብ አማልክት ላይ እንደሚናገሩ መጠን በኢየሩሳሌም አምላክ ላይ ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሰው እጅ በሠራቸው በሌሎች የምድር አሕዛብ አማልክት ላይ እንደ ተናገሩት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም አምላክ ላይም ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በሰው እጅ በተሠሩ በሌሎች ሕዝቦች የጣዖት አማልክት ላይ በድፍረት በተናገሩት ዐይነት በኢየሩሳሌም አምላክ ላይም ይናገሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በሰ​ውም እጅ በተ​ሠሩ በም​ድር አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ላይ እን​ደ​ሚ​ና​ገር መጠን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አም​ላክ ላይ ተና​ገረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በሰውም እጅ በተሠሩ በምድር አሕዛብ አማልክት ላይ አንደሚናገሩ መጠን በኢየሩሳሌም አምላክ ላይ ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 32:19
31 Referencias Cruzadas  

ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸው ላበጇቸው፤ ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ።


ከእንጨትና ከድንጋይ ተጠርበው የተሠሩ የሰው እጅ ሥራ እንጂ አማልክት ስላልነበሩ በእሳት ላይ ጥለው አጠፉአቸው።


ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፤ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥


የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች ከታናሽነታቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ ነገርን ብቻ አድርገዋልና፤ የእስራኤልም ልጆች እኔን በእጃቸው ሥራ ከማስቈጣት በቀር ሌላ ሥራ አላደረጉምና፥ ይላል ጌታ።


የሞያተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ሐምራዊ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው።


የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሞያተኛውም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።


ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ፥ እኔን ትተውኛል፤ ለሌሎችም አማልክት ዕጣንን አጥነዋል፤ ለእጃቸውም ሥራዎች ሰግደዋልና።


አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ፥ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።


ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መልስ ይሰጣል? “ጌታ ጽዮንን መሥርቷል፥ ከሕዝቡም ችግረኞች በእርሷ ውስጥ መጠጊያን ያገኛሉ።”


የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፥ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ።’


ባርያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።


“‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


በዚያም ማየትም ሆነ መስማት፥ መብላት ሆነ ማሽተት የማይችሉትን፥ በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት ታመልካላችሁ።


ንጉሡም ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ነገር ጸለዩ፥ ወደ ሰማይም ጮኹ።


አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ሶርያውያን ጌታ የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም’ ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃላችሁ” አለው።


ይህንንም አስታውስ፥ ጠላት በጌታ ተሳለቀ፥ አላዋቂ ሕዝብም በስምህ ቀለደ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሞአብና ሴይር፦ እነሆ የይሁዳ ቤት እንደ ሌሎች ሕዝቦች ነው ብለዋልና፥


በአፋችሁ ታበያችሁብኝ፥ ንግግራችሁንም በእኔ ላይ አበዛችሁ፤ እኔም ሰምቼዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios