2 ዜና መዋዕል 33:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተ ውጭው ከግዮን ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሳ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። በዖፌልም አዞረበት፥ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ በሸለቆው ውስጥ ከሚገኘው ከግዮን ምንጭ ምዕራብ አንሥቶ እስከ ዓሣ በር መግቢያ ድረስ ያለውን የዳዊትን ከተማ የውጭውን ቅጥር፣ የዖፌልን ኰረብታ እንዲከብብ በማድረግ፣ ይበልጥ ከፍ አድርጎ እንደ ገና ሠራው። በተመሸጉትም የይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጦር አዛዦችን አኖረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ምናሴ በዳዊት ከተማ በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን የውጪ ቅጽር ቁመት ከፍ አድርጎ ሠራ፤ ይህም ቅጽር በሸለቆው ውስጥ ከግዮን ምንጭ በስተ ምዕራብ በኩል አንሥቶ፥ በስተ ሰሜን እስከ ዓሣ ቅጽር በር የሚደርስ ሲሆን፥ በከተማይቱ አጠገብ የሚገኘውን ዖፌል ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ የሚያጠቃልል ነው፤ እንዲሁም ምናሴ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ፥ ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ የክፍለ ጦር አዛዥ መደበላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዓለምን ሁሉ የምትገዛ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ፥ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ፥ ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተ ውጭው ከግዮን ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሳ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። በዖፌልም አዞረበት፤ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ። |
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፥ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፥ ከተማይቱም አስተጋባች፥ የሰማችሁትም ድምፅ ይህ ነው።
ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፥ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ።
ንጉሥ ሕዝቅያስም ራሱን ለሥራ ጽኑ አደረገ፥ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፥ በላዩም ግንብ ሠራበት፥ ከእርሱም በስተ ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ በዳዊትም ከተማ ያለችውን ሚሎን አጠነከረ፤ ብዙም የጦር መሣሪያና ጋሻ ሠራ።
ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
አዳራሹ ወና ይሆናል፥ በሰው የተጨናነቀውም ከተማ ወና ይሆናል፤ ምሽጉና ግንቡም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናል።