Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 33:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ወደ እርሱም ጸለየ፤ እርሱም ተለመነው፥ ጸሎቱንም ሰማው፥ ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው፤ ምናሴም እርሱ ጌታ አምላክ እንደሆነ አወቀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ወደ እርሱም በጸለየ ጊዜ፣ በጭንቀት ልመናው ራርቶለት እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው። ስለዚህ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ መንግሥቱም መለሰው፤ ምናሴም እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዐወቀ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔርም የምናሴን ጸሎት ሰማ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመልሶ እንደገና እንዲገዛ ፈቀደለት፤ በዚህም ምናሴ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ መሆኑን ተገነዘበ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምና​ሴም ጸለየ እን​ዲ​ህም አለ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ወደ እርሱም ጸለየ፤ እርሱም ተለመነው፤ ጸሎቱንም ሰማው፤ ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው፤ ምናሴም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ አወቀ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 33:13
41 Referencias Cruzadas  

ጾምን፥ አምላካችንን ስለዚህ ነገር ለመንን፤ እርሱም ልመናችንን ሰማ።


በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ እነርሱንም ረዳቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተላልፈው ተሰጡ።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፥ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና፥ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።


አቤቱ፥ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህና፥ ጽኑ ፍቅርህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።


እያንዳንዱም ‘ጌታን እወቅ፥’ ብሎ ጐረቤቱን ወይም ወንድሙን አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና።


የዘለዓለም ሕይወትም ይህች ናት፤ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንከውን አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ነው።


ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ወሃ አጠጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ፥ አንቺ በለመንሽው ነበር፤ የሕይወትም ውሃ በሰጠሽ ነበር፤” አላት።


እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ያስቆማል፥ ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቆራርጣል፥ በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል።


አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።


ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥ ስእለትህንም ትሰጣለህ።


ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ ትደረጃለህ፥ ክፋትንም ከድንኳንህ ብታርቅ፥


በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት እንዲያሳምር እንደዚህ ያለውን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥ የአባቶቻችን አምላክ ጌታ ይባረክ።


ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።


የሰው አካሄድ ጌታን ደስ ያሰኘው እንደሆነ፥ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል።


ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርሷ ወደ ጌታ ጸለየ፤ ጌታም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤


የምናሴም የቀረው ነገር፥ ወደ አምላኩም የጸለየው ጸሎት፥ በእስራኤልም አምላክ በጌታ ስም የነገሩት የነቢያት ቃላት፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።


ደግሞም ጸሎቱ፥ ጌታም እንደ ተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሠራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።


ጌታ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በጌታ ፊት ይቀርብ ይሆናል፥ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።”


ኃጢአታቸውንና አንተን ያሳዘኑበትን ዐመፅ ሁሉ ይቅር በል፤ ጠላቶቻቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ፤


ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ “ጌታ አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው!” አሉ።


ከዚህ በኋላ ኢዮአካዝ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ የፈጸመባቸው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ተመልክቶ የኢዮአካዝን ጸሎት ሰማ።


ጌታም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ የጌታ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሸማያ መጣ፦ “ራሳቸውን አዋርደዋል፤ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፥ ቁጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይወርድም፤


ልብህ ተጸጽቶአልና፥ በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራና በነዋሪዎችዋ ላይ የተናገርሁትን ቃላቴን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


ከአፉም ትምህርቱን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፥


ተግባራቸውንና መተላለፋቸውን በትዕቢትም እንደሚሠሩም ይናገራቸዋል።


ከሰሙትና ካገለገሉት፥ ዕድሜአቸውን በብልጽግና፥ ዘመናቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ።


ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።


ድምፄን ሰማህ፥ ጆሮህን ከልመናዬ አትመልስ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios