Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 17:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሡ በተመሸጉ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካኖራቸውም ሌላ እነዚህ ንጉሡን ያገለግሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነዚህ ሁሉ ወታደሮች ንጉሥ ኢዮሣፍጥን በኢየሩሳሌም የሚያገለግሉ ሲሆኑ፥ በተጨማሪም ንጉሡ በሌሎቹ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሌሎች ወታደሮችን አስፍሮ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ንጉሡ በተ​መ​ሸጉ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ካኖ​ራ​ቸ​ውም ሌላ እነ​ዚህ ንጉ​ሡን ያገ​ለ​ግሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ንጉሡ በተመሸጉ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካኖራቸውም ሌላ እነዚህ ንጉሡን ያገለግሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 17:19
6 Referencias Cruzadas  

በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፥ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ።


ኢዮሣፍጥም እየበረታና እጅግም እየከበረ ሄደ፤ በይሁዳም ግንቦችንና ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሠራ።


ተጠበበም፥ ልጆቹንም ሁሉ በይሁዳና በብንያም አገር ሁሉ በተመሸጉትም ከተሞች ሁሉ ከፋፈላቸው፤ ብዙም ስንቅ ሰጣቸው፤ ብዙም ሚስቶች ፈለገላቸው።


በከተሞቹ ሁሉ ጋሻና ጦርን አኖረ። ከተሞቹንም እጅግ አጠነከራቸው፤ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ።


ከእርሱም በኋላ ዩዛባት፥ ከእርሱም ጋር ለጦርነት የተዘጋጁ መቶ ሰማኒያ ሺህ ሰዎች ነበሩ።


ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተ ውጭው ከግዮን ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሳ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። በዖፌልም አዞረበት፥ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios