2 ዜና መዋዕል 32:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማይቱ በስተ ውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ለመድፈን ከሹማምንቱና ከኃያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከከተማዪቱ ውጭ ያሉት የውሃ ምንጮች እንዲዘጉ ከሹማምቱና ከጦር አለቆቹ ጋራ ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ከባለሟሎቹ ባለሥልጣኖች ጋር ከከተማይቱ ውጪ ያሉትን ምንጮችና የውሃ መተላለፊያ ቦይ ለመድፈን ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት፤ ይህንንም ያደረጉት አሦራውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረቡ ምንም ውሃ እንዳያገኙ ለማድረግ ነው፤ ስለዚህ ባለሥልጣኖቹ ብዙ ሰዎችን ወደዚያ በመውሰድ ከምንጮቹ ውሃ እንዳይፈስስ ለማድረግ፥ እነዚያን ምንጮች ሁሉ ደፈኑአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከከተማዪቱ በስተውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ይደፍኑ ዘንድ ከአለቆቹና ከኀያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ምክሩን ወደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማይቱ በስተ ውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ይደፍኑ ዘንድ ከአለቆቹና ከኃያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት። |
ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፥ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቆፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።
ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፥ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ።
እጅግም ሰዎች ተሰብስበው፦ “የአሦር ነገሥታት መጥተው ብዙ ውኃ ለምን ያገኛሉ?” ብለው ምንጩን ሁሉ፥ በምድርም መካከል ይንዶለዶል የነበረውን ዥረት ደፈኑ።