Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 32:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3-4 እርሱ ከባለሟሎቹ ባለሥልጣኖች ጋር ከከተማይቱ ውጪ ያሉትን ምንጮችና የውሃ መተላለፊያ ቦይ ለመድፈን ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት፤ ይህንንም ያደረጉት አሦራውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረቡ ምንም ውሃ እንዳያገኙ ለማድረግ ነው፤ ስለዚህ ባለሥልጣኖቹ ብዙ ሰዎችን ወደዚያ በመውሰድ ከምንጮቹ ውሃ እንዳይፈስስ ለማድረግ፥ እነዚያን ምንጮች ሁሉ ደፈኑአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከከተማዪቱ ውጭ ያሉት የውሃ ምንጮች እንዲዘጉ ከሹማምቱና ከጦር አለቆቹ ጋራ ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከከተማይቱ በስተ ውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ለመድፈን ከሹማምንቱና ከኃያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ውጭ ያለ​ውን የው​ኃ​ውን ምንጭ ይደ​ፍኑ ዘንድ ከአ​ለ​ቆ​ቹና ከኀ​ያ​ላኑ ጋር ተማ​ከረ፤ እነ​ር​ሱም ምክ​ሩን ወደዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከከተማይቱ በስተ ውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ይደፍኑ ዘንድ ከአለቆቹና ከኃያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 32:3
13 Referencias Cruzadas  

ለጦርነት ከመሰለፍህ በፊት በጥንቃቄ ዕቅድ ማውጣት ይኖርብሃል፤ ብዙ አማካሪዎች የምታገኝ ከሆነም ማሸነፍህ አይቀርም።


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ስለዚህ መልካም ምክር ሳትቀበል ወደ ጦርነት አትሂድ።


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ምክርን ባትቀበል ግን ምንም ነገር አይሳካልህም።


“የጌታን አሳብ የሚያውቅ ማነው? የእርሱ አማካሪ የሚሆንስ ማነው?


እግዚአብሔርን “እንዲህ አድርግ” ብሎ የሚያዘው ማን ነው? እርሱን ማስተማርና መምከር የሚችልስ ማን ነው?


ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፥ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቈፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


የቃላት ጋጋታ የጦርነትን ስልትና ኀይል የሚተካ ይመስልሃልን? ማን ይረዳኛል ብለህ ነው በአሦር ላይ ለማመፅ ያሰብከው?


ሰናክሬም በኢየሩሳሌምም ላይ አደጋ ለመጣል ያቀደ መሆኑን ንጉሥ ሕዝቅያስ በተገነዘበ ጊዜ፥


ጠላቶችሽ ከበው በሚያስጨንቁሽ ጊዜ የምትጠጪውን ውሃ ቀድተሽ አዘጋጂ! ምሽጎችሽን አጠናክሪ! ጭቃ ረግጠሽ የሸክላ መሥሪያ አዘጋጂ! ጡብም ሥሪ።


በላይ በኩል ያለውን የግዮንን ምንጭ መውጫ ገድቦ ውሃውን ወደ ምዕራብ፥ ወደ ዳዊት ከተማ፥ በቦይ እንዲወርድ ያደረገ ራሱ ሕዝቅያስ ነው፤ ይህ ሕዝቅያስ ሊሠራ ባቀደው ነገር ሁሉ የተሳካለት ሰው ነበር፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios