Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 32:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እጅግም ሰዎች ተሰብስበው፦ “የአሦር ነገሥታት መጥተው ብዙ ውኃ ለምን ያገኛሉ?” ብለው ምንጩን ሁሉ፥ በምድርም መካከል ይንዶለዶል የነበረውን ዥረት ደፈኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው “የአሦር ነገሥታት መጥተው ስለ ምን ብዙ ውሃ ያገኛሉ?” በማለት ምንጮቹን ሁሉና በምድር ውስጥ ለውስጥ ይተላለፍ የነበረውን ውሃ ዘጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ብዙ ሰዎ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፥ “የአ​ሦ​ርም ንጉሥ እን​ዳ​ይ​መ​ጣና ብዙ ውኃ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ጠ​ነ​ክር” ብሎ የውኃ ምን​ጮ​ች​ንና በከ​ተ​ማ​ዪቱ የሚ​ፈ​ስ​ሱ​ትን ወን​ዞች ደፈነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እጅግም ሰዎች ተሰብስበው “የአሦር ነገሥታት መጥተው ብዙ ውኃ ስለ ምን ያገኛሉ?” ብለው ምንጩን ሁሉ፥ በምድርም መካከል ይንዶለዶል የነበረውን ወንዝ ደፈኑ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 32:4
15 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ ዐረዳቸው፤ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ።


ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በትክክለኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”


ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም አደጋ በመጣል የተመሸጉትን የይሁዳን ከተሞች ያዘ፤


ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ይህም ማለት ሆሴዕ በእስራኤል በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር በእስራኤል ላይ አደጋ በመጣል ሰማርያን ከበበ፤


እግዚአብሔር ሆይ፥ የአሦር ነገሥታት ብዙ ሕዝቦችና ምድራቸውን መደምሰሳቸው እርግጥ ነው።


ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፥ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቆፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


ተነሥተውም በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና ለጣዖታት የሚያጥኑበትን ዕቃ ሁሉ አስወገዱ፥ በቄድሮንም ወንዝ ጣሉት።


ከዚህም ነገርና በታማኝነት ከተደረገው ነገር በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፥ በተመሸጉትም ከተሞች ፊት ሰፈረ፥ የራሱም ሊያደርጋቸው አሰበ።


ከከተማይቱ በስተ ውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ለመድፈን ከሹማምንቱና ከኃያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት።


ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፥ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ።


እንዲህም ይል ነበር፤ “የጦር አዛዦቹ በሙሉ ነገሥታት አይደሉምን?


በአሮጌው ኩሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፥ ቀድሞ አቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።


የዳዊትም ከተማ ፍራሾች እንደበዙ አይታችኋል፥ የታችኛውንም ኩሬ ውኃ አጠራቅማችኋል።


ለከበባው ውኃ ለራስሽ ቅጂ፥ ምሽግሽን አጠናክሪ፤ ወደ ጭቃው ግቢ፥ ጭቃውንም ርገጪ፥ የጡብ መሥሪያ ያዢ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos