La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 31:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በየከተማይቱም ሁሉ በከተማቸው መሰማሪያዎች ውስጥ ላሉ ለአሮን ልጆች ለካህናቱ፥ ከካህናቱም ወገን ላሉ ወንዶች ሁሉ፥ በትውልዳቸውም ለተቈጠሩ ሌዋውያን ሁሉ ድርሻቸውን እንዲሰጡአቸው በስማቸው የተጻፉ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በከተሞቻቸው ዙሪያ ባሉት የዕርሻ ቦታዎች፣ ወይም በሌሎች ከተሞች ሁሉ ለሚኖሩት ለካህናቱ ለአሮን ዘሮች፣ በመካከላቸው ላሉት ወንዶችና በሌዋውያን የትውልድ መዝገብ ለተመዘገቡት ሁሉ እንዲያከፋፍሉ በየስማቸው የተጻፉ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለአሮን ልጆች በተመደቡ ከተሞች ወይም የእነዚህ ከተሞች ይዞታ በሆኑት የግጦሽ ቦታዎች ከሚኖሩት ካህናት መካከል ለካህናት ቤተሰቦችና በሌዋውያን ጐሣ የስም ዝርዝር በያዘ መዝገብ ውስጥ ስማቸው ለሚገኝ ወንዶች ሁሉ ምግብን ለማከፋፈል ኀላፊዎች የሆኑ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ክህ​ነት ለሚ​ገ​ባ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ዙሪያ ባሉ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችና በሌ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ላሉ ለወ​ን​ዶች ሁሉ፥ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋራ ለተ​ቈ​ጠሩ ሰዎ​ችም ሁሉ ከፍ​ለው ይሰጡ ዘንድ በስም የተ​ጠሩ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በየከተማይቱም ሁሉ በከተማቸው መሰማርያቹ ላሉ ለአሮን ልጆች ለካህናቱ፥ ከካህናቱም ወገን ላሉ ወንዶች ሁሉ፥ በትውልዳቸውም ለተቈጠሩ ሌዋውያን ሁሉ ክፍላቸውን ይሰጡ ዘንድ በስማቸው የተጻፉ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 31:19
8 Referencias Cruzadas  

ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ አንደኛው ዕጣ የወጣው ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች ነበረ።


እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።


በስማቸውም የተጻፉ ሰዎች ተነሥተው ምርኮኞቹን ወሰዱ፥ በመካከላቸውም ራቁታቸውን ለነበሩት ሁሉ ከምርኮው አለበሱአቸው፥ አጎናጸፉአቸውም፥ ጫማም በእግራቸው አደረጉላቸው፥ መገቡአቸውም፥ አጠጡአቸውም፥ ቀቡአቸውም፤ ደካሞቹንም ሁሉ በአህዮች ላይ አስቀመጡአቸው፥ ዘንባባም ወዳለበት ከተማ ወደ ኢያሪኮ ወደ ወንድሞቻቸው አመጡአቸው፤ ወደ ሰማሪያም ተመለሱ።


በታማኝነትም ቅድስናቸውን ጠብቀዋልና ካህነናቱ በየትውልዳቸው ከሕፃናቶቻቸውና ከሚስቶቻቸው ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው እንዲሁም ከማኅበሩ ሁሉ ጋር ተቈጠሩ።


ነገር ግን ለሌዋውያን ርስታቸው በሆኑት በሌዋውያን ከተሞች ውስጥ ያሉትን ቤቶች ለዘለዓለም የመቤዠት መብት አላቸው።


በከተማቸውም ዙሪያ ያለው መሰማሪያ የዘለዓለም ርስታቸው ነውና አይሸጥም።