Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 31:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በታማኝነትም ቅድስናቸውን ጠብቀዋልና ካህነናቱ በየትውልዳቸው ከሕፃናቶቻቸውና ከሚስቶቻቸው ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው እንዲሁም ከማኅበሩ ሁሉ ጋር ተቈጠሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በዚህ የትውልድ መዝገብ ላይ የተዘረዘሩትን መላውን የማኅበረ ሰቡን ሕፃናት፣ ሚስቶችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ጨመሯቸው፤ ራሳቸውን በመቀደስ ታማኞች ነበሩና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነዚህ ካህናትና ሌዋውያን ራሳቸውን የቀደሱ ታማኞች ስለ ነበሩ የሚመዘገቡት ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸውና በእነርሱ ሥር ከሚተዳደሩት ሰዎች ሁሉ ጋር በአንድነት ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በማ​ኅ​በ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ለሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ይሰጡ ነበር፤ በእ​ም​ነት ፈጽ​መው ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በማኅበሩም ሁሉ በየትውልዳቸው ለተቈጠሩ ለሕፃናቶቻቸውና ለሚስቶቻቸው ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸውም ይሰጡ ነበር፤ በእምነት ተቀድሰዋልና።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 31:18
6 Referencias Cruzadas  

የመግቢያው ደጅ ጠባቂዎች እንዲሆኑ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ።


በካህናቱም ከተሞች ለታላላቆችና ለታናናሾች ወንድሞቻቸው በየሰሞናቸው ድርሻቸውን በታማኝነት እንዲሰጡ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሸማያ፥ አማርያ፥ ሴኬንያ የቆሬ ረዳቶች ነበሩ።


በየአባቶቻቸውም ቤት ካህናቱ ተቈጠሩ፤ በየሥርዓታቸውና በየሰሞናቸው ዕድሜያቸው ሀያ ዓመት የሆናቸውና ከዚያ በላይ የሆኑ ሌዋውያኑ ተቈጠሩ።


በየከተማይቱም ሁሉ በከተማቸው መሰማሪያዎች ውስጥ ላሉ ለአሮን ልጆች ለካህናቱ፥ ከካህናቱም ወገን ላሉ ወንዶች ሁሉ፥ በትውልዳቸውም ለተቈጠሩ ሌዋውያን ሁሉ ድርሻቸውን እንዲሰጡአቸው በስማቸው የተጻፉ ሰዎች ነበሩ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።


በእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው፥ ይህም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos