Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 28:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በስማቸውም የተጻፉ ሰዎች ተነሥተው ምርኮኞቹን ወሰዱ፥ በመካከላቸውም ራቁታቸውን ለነበሩት ሁሉ ከምርኮው አለበሱአቸው፥ አጎናጸፉአቸውም፥ ጫማም በእግራቸው አደረጉላቸው፥ መገቡአቸውም፥ አጠጡአቸውም፥ ቀቡአቸውም፤ ደካሞቹንም ሁሉ በአህዮች ላይ አስቀመጡአቸው፥ ዘንባባም ወዳለበት ከተማ ወደ ኢያሪኮ ወደ ወንድሞቻቸው አመጡአቸው፤ ወደ ሰማሪያም ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በስም የተጠቀሱ ሰዎችም ምርኮኞቹን ተረክበው ዕራቍታቸውን ለቀሩት ሁሉ ከምርኮው አለበሷቸው፤ ልብስና ጫማ፣ ምግብና መጠጥ ሰጧቸው፣ በቅባትም ቀቧቸው፤ የደከሙትንም ሁሉ በአህያ ላይ አስቀመጧቸው። ከዚያም ወገኖቻቸው ወደሚገኙባት የዘንባባ ከተማ ተብላ ወደምትጠራው ወደ ኢያሪኮ ወስደዋቸው፣ ወደ ሰማርያ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚያም በኋላ እነዚያ አራት ሰዎች ለእስረኞቹ ከምርኮው አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲሰጡ ተመደቡ፤ እነርሱም ራቊታቸውን ለቀሩት እስረኞች ልብስና ጫማ፥ እንዲሁም በቂ ምግብና ውሃ ሰጡአቸው፤ በቊስላቸውም ላይ የወይራ ዘይት በማፍሰስ ርዳታ አደረጉላቸው፤ በእግር ለመሄድ የማይችሉትን ደካሞችንም በአህያ ላይ አስቀመጡአቸው፤ እስረኞቹም ሁሉ በይሁዳ ግዛት ወደምትገኘው፥ የዘንባባ ዛፍ በብዛት ወደሚገኝባት ወደ ኢያሪኮ ከተማ መልሰው ወሰዱአቸው፤ ከዚህም በኋላ እስራኤላውያን ወደ መኖሪያ ከተማቸው ወደ ሰማርያ ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በስ​ማ​ቸ​ውም የተ​ጻፉ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ምር​ኮ​ኞ​ቹን ወሰዱ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ራቁ​ታ​ቸ​ውን ለነ​በ​ሩት ሁሉ ከም​ር​ኮው አለ​በ​ሱ​አ​ቸው፤ አጐ​ና​ጸ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ ጫማም በእ​ግ​ራ​ቸው አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው፤ መገ​ቡ​አ​ቸ​ውም፤ አጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ቀቡ​አ​ቸ​ውም፤ ደካ​ሞ​ቹ​ንም ሁሉ በአ​ህ​ዮች ላይ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው፤ ዘን​ባ​ባም ወዳ​ለ​በት ከተማ ወደ ኢያ​ሪኮ ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በስማቸውም የተጻፉ ሰዎች ተነሥተው ምርኮኞቹን ወሰዱ፤ በመካከላቸውም ራቁታቸውን ለነበሩት ሁሉ ከምርኮው አለበሱአቸው፤ አጎናጸፉአቸውም፤ ጫማም በእግራቸው አደረጉላቸው፤ መገቡአቸውም፤ አጠጡአቸውም፤ ቀቡአቸውም፤ ደካሞቹንም ሁሉ በአህዮች ላይ አስቀመጡአቸው፤ ዘንባባም ወዳለበት ከተማ ወደ ኢያሪኮ ወደ ወንድሞቻቸው አመጡአቸው፤ ወደ ሰማሪያም ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 28:15
21 Referencias Cruzadas  

ኤልሳዕም “አይሆንም! እንኳን እነዚህን፥ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኻቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ” አለው።


ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ።


ደግሞም ከኤፍሬም ልጆች አለቆች የዮሐናን ልጅ ዓዛርያስ፥ የምሺሌሞትም ልጅ በራክያ፥ የሰሎምም ልጅ ይሒዝቅያ፥ የሐድላይም ልጅ ዓሜሳይ ከጦርነት በተመለሱት ላይ ተቃወሙአቸው።


ተዋጊዎቹም ምርኮኞቹንና ምርኮውን በአለቆችና በጉባኤው ሁሉ ፊት ተው።


የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት።


እነርሱም፦ “እንመልስላቸዋለን፥ ከእነርሱም ምንም አንፈልግም፤ አንተ እንዳልኸው እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ ቃል እንደገቡት እንዲያደርጉ አስማልኳቸው።


እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?


“ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፤


እርሱም ወደ ምድር እንደ ወረደ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ለረጅም ጊዜ ልብስ አይለብስም ነበር፥ በመቃብሮች እንጂ በቤት ውስጥም አይኖርም ነበር።


ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ፥ ልቡም ተመልሶ፥ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።


ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነት አወጡት፤ መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ።


እኛ ብርቱዎች የሆንን የደካሞችን ድካም መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።


እስከ ጾዓር ድረስ ያለውንም የዘንባባ ዛፎች ያሉባትን ከተማ የኢያሪኮን ሸለቆ ሜዳ አሳየው።


እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos