መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፥ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን።” ዳዊትም ተቀበላቸው፥ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
2 ዜና መዋዕል 26:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን በምዑናውያንም ላይ ረዳው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን፣ በጉርበኣል በሚኖሩ ዐረቦችና በምዑናውያን ላይ ድልን አቀዳጀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያንን፥ በጒርባዓል ይኖሩ የነበሩትን ዐረቦችና መዑናውያንን ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ረዳው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በዓለት ላይ በሚኖሩ ዓረባውያን፥ በምዕዑናውያንም ላይ አጸናው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን በምዑናውያንም ላይ ረዳው። |
መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፥ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን።” ዳዊትም ተቀበላቸው፥ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ።
በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ እነርሱንም ረዳቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተላልፈው ተሰጡ።
አሳም እንዲህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህምና፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ! በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ።”
ከፍልስጥኤማውያንም ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻና የብር ግብር ያመጡ ነበሩ፤ ዓረባውያንም ደግሞ ከመንጎቻቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየሎች ያመጡለት ነበር።
ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ ይሆን ዘንድ ያለውን፥ ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በሙታንም ትንሣኤ ለሕዝብና ለአሕዛብ ብርሃንን በመጀመሪያ ሊሰብክ እንዳለው፥ ከተናገሩት በቀር አንድ ስንኳ የተናገርሁት የለም።”