ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤
2 ዜና መዋዕል 26:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀረውንም የፊተኛውንና የኋለኛውን የዖዝያንን ነገር ነቢዩ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ጽፎታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዖዝያን ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የተከናወነውን ሌላውን ተግባር ሁሉ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ጽፎታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዖዝያ በዘመነ መንግሥቱ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ መዝግቦት ይገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የዖዝያን ነገሮች በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ ተጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውንም የፊተኛውንና የኋለኛውን የዖዝያንን ነገር ነቢዩ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ጽፎታል። |
ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤
የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራእዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ጦርነት ነበረ።
ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ እነርሱም፦ “ለምጻም ነው” ብለው ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ተግባራት በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ በቃላት የተጻፈ አይደለምን?