Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ተግባራት በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ በቃላት የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የቀረው፣ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ሥራ፣ ጥበቡም በነቢዩ በናታን ታሪክና በሴሎናዊው በአኪያ ትንቢት እንዲሁም ባለራእዩ አዶ ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው ራእይ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሌላው የሰሎሞን ታሪክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በነቢዩ ናታን ታሪክ፥ የሴሎ ተወላጅ በሆነው በነቢዩ አኪያ ትንቢትና ስለ እስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ጭምር በሚናገረው በነቢዩ ዒዶ ራእይ ተመዝግቦ ይገኛል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የቀ​ረ​ውም ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው የሰ​ሎ​ሞን ነገር በነ​ቢዩ በና​ታን ታሪክ፥ በሴ​ሎ​ና​ዊ​ውም በአ​ኪያ ትን​ቢት፥ ስለ ናባ​ጥም ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢ​ዩ​ሔል ራእይ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:29
15 Referencias Cruzadas  

ጌታ ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ሀብታም ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ ድኻ ነበረ።


ጌታ ሕፃኑን ስለ ወደደም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያ፥ ነቢዩም ናታን፥ ሺምዒና ሬዒ፥ የዳዊትም ተዋጊዎች ከአዶንያስ ጋር አልነበሩም።


በሰሎሞን ላይ ያመፀው ሌላው ሰው በኤፍሬም ጸሬዳ ተብላ የምትጠራው ክፍለ ሀገር ተወላጅ የሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነው፤ እርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች አንዱ ነበር፤ እናቱም ጽሩዓ ተብላ የምትጠራ ባሏ የሞተባት ሴት ነበረች።


አንድ ቀን ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በጉዞ ላይ ሳለ አዲስ መጐናጸፊያ የለበሰ፥ ከሴሎ የመጣው ነቢዩ አኪያ ከከተማ ውጪ መንገድ ላይ ብቻውን አገኘው።


ስለዚህ ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “የእኔ ሚስት መሆንሽን ማንም እንዳያውቅ ልብስሽን ለውጠሽ ሌላ ሴት በመምሰል እኔ የእስራኤል ንጉሥ እንደምሆን የትንቢት ቃል የተናገረው ነቢዩ አኪያ ወደሚኖርባት ወደ ሴሎ ሂጂ።፤


የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።


የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ሸሽቶ በግብጽ ይኖር ነበርና ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመለሰ።


የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራእዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ጦርነት ነበረ።


የአብያም የቀረው ነገርና አካሄዱ የተናገራቸውም ቃሎች በነቢዩ በአዶ መጽሐፍ ተጽፈዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos