ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል።
2 ዜና መዋዕል 26:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያን ሆይ! ዕጣን ማጠን የተቀደሱት የአሮን ልጆች የካህናቱ ሹመት ነው እንጂ ለጌታ እንድታጥን ለአንተ አይገባህም፤ በድለሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከአምላክህም ከጌታ ዘንድ ክብር አያስገኝልህም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ፊት ለፊት በመጋፈጥ፣ “ዖዝያን ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ማጠን ለተለዩትና የአሮን ዘሮች ለሆኑት ለካህናቱ እንጂ ለአንተ የተገባ አይደለም፤ እግዚአብሔርን አልታመንህምና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከእግዚአብሔር አምላክ ዘንድም ክብር አይሆንልህምና” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ! አንተ ለእግዚአብሔር ዕጣን ታጥን ዘንድ አይገባህም፤ ይህን ለማድረግ የተመደቡት ለእግዚአብሔር የተለዩት የአሮን ልጆች የሆኑት ካህናት ብቻ ናቸው፤ ስለዚህ ከዚህ ከተቀደሰው ስፍራ ውጣ፥ እግዚአብሔር አምላክን አሳዝነሃል፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን የሚያስገኝልህ ድርጊት አይደለም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ፥ “ዖዝያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተቀደሱት ለአሮን ልጆች ለካህናቱ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር ታጥን ዘንድ ለአንተ አይገባህም፤ ከእግዚአብሔር ርቀሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ይህም በአምላክ በእግዚአብሔርም ዘንድ ለአንተ ክብር አይሆንህም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ “ዖዝያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን የተቀደሱት የአሮን ልጆች የካህናቱ ሹመት ነው እንጂ ለእግዚአብሔር ታጥን ዘንድ ለአንተ አይገባህም፤ በድለሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከአምላክህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብር አይሆንልህም” አሉት። |
ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል።
እናንተም እንደምታዩት መሣቀቅያ እስኪያደርጋቸው ድረስ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን እንደ በደሉ እንደ አባቶቻችሁና እንደ ወንድሞቻችሁ አትሁኑ።
ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት እንዲሆኑልኝ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን አቅርብ።
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።