ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በጌታ ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም በእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።
2 ዜና መዋዕል 23:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉባኤውም ሁሉ በጌታ ቤት ውስጥ ከንጉሥ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ ጌታ ስለ ዳዊት ልጆች እንደ ተናገረ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጉባኤው ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ከንጉሡ ጋራ ቃል ኪዳን አደረጉ። ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ለዳዊት ዘር በሰጠው ተስፋ መሠረት እነሆ፤ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም በአንድነት በቤተ መቅደሱ ተሰብስበው ከንጉሡ ልጅ ከኢዮአስ ጋር የስምምነት ውል አደረጉ፤ ካህኑ ዮዳሄ እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር ለዳዊት ‘ልጆችህ ለዘለቄታ ይነግሣሉ’ ሲል በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት አሁን መንገሥ ያለበት ኢዮአስ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ጉባኤ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከንጉሥ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። የንጉሥንም ልጅ አሳያቸው፤ አላቸውም፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ቤት እንደ ተናገረ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጉባኤውም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከንጉሥ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ዮዳሄም አላቸው “እነሆ፥ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ልጆች እንደተናገረ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል። |
ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በጌታ ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም በእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።
ዕድሜህን ጨርሰህ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ፥ በእግርህ እንዲተካ ከአብራክህ የተከፈለ ዘር አስነሣልሃለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።
በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ ጌታ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።
ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ፥ ዙፋንህ በእስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።
ዮዳሄ፥ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ።
የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በጌታ ፊት ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ በሳሙኤልም አንደበት እንደ ተናገረው እንደ ጌታ ቃል በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።
ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ለመስጠት ስላደረገው ተስፋ፥ ጌታ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም።
እንግዲህ አሁን፥ አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ‘አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆችህ በሕጌ እንዲሄዱ መንገዳቸውን ቢጠብቁ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው በፊቴ አታጣም’ ብለህ ተስፋ የሰጠኸውን ለባርያህ ለአባቴ ለዳዊት ጠብቅ።