Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ፥ ዙፋንህ በእስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለአባትህ ለዳዊት፣ ‘በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዘርህ አታጣም’ በማለት በሰጠሁት ተስፋ መሠረት ዙፋንህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ፥ ዙፋንህ በእስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እኔ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የሚ​ገዛ ሰውን ከአ​ንተ አላ​ጠ​ፋም ብዬ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት እንደ ተና​ገ​ርሁ፥ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህን ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እኔ ‘ከእስራኤል ዙፋን ከዘርህ ሰው አታጣም፤’ ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 9:5
9 Referencias Cruzadas  

ዕድሜህን ጨርሰህ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ፥ በእግርህ እንዲተካ ከአብራክህ የተከፈለ ዘር አስነሣልሃለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።


ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘለዓለም የጸና ይሆናል።’ ”


በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ ጌታ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።


“ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት ሕጎቼን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቴን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል ለአንተ አጸናለሁ።


እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦


“እነሆ ጌታ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህም እኔ በአባቴ ቦታ ተተክቼ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀመጥኩ፤ ጌታም ቃል እንደገባው፥ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ለስሙ ቤት ሠራሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos