2 ዜና መዋዕል 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት ግን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደች፤ እርሱንና ሞግዚቱን በእልፍኝ ውስጥ አኖረቻቸው፤ ጎቶሊያ እንዳታስገድለው የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት እንዲሁ ሸሸገችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ኢዮራም ልጅ ዮሳቤት ግን፣ ሊገደሉ ከነበሩት ልዑላን መካከል ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደችው፤ እንዳይገድሉትም እርሱንና ሞግዚቱን በአንድ እልፍኝ ሸሸገቻቸው። የኢዮሆራም ልጅና የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት፣ የአካዝያስ እኅት በመሆኗ፣ ሕፃኑን የደበቀችው ጎቶልያ እንዳትገድለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አካዝያስ፥ ይሆያዳዕ ተብሎ የሚጠራውን ካህን ያገባች ይሆሼባዕ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ እርስዋም ከአካዝያስ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነውን ኢዮአስን ሊገድሉ ጥቂት ቀርቶአቸው ከነበሩት መሳፍንት መካከል በስውር ወስዳ እርሱንና ሞግዚቱን በቤተ መቅደስ አጠገብ በሚገኝ መኝታ ቤት ውስጥ ደበቀቻቸው፤ በዚህም ዐይነት በመደበቅ ኢዮአስን በዐታልያ እጅ ከመገደል አዳነችው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት ግን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደች፤ እርሱንና ሞግዚቱን በእልፍኝ ውስጥ አኖረቻቸው፤ የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት ከጎቶልያ ፊት ሸሸገችው፤ እርስዋም አልገደለችውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት ግን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደች፤ እርሱንና ሞግዚቱን በእልፍኝ ውስጥ አኖረቻቸው፤ ጎቶሊያ እንዳታስገድለው የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት እንዲሁ ሸሸገችው። |
ይሁን እንጂ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም በሰላም እንዲጠብቅ ጌታ አምላኩ ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው።
ከእርሷም እጅ ማምለጥ የቻለ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ ብቻ ነበር፤ እርሱም እንኳ ከሌሎቹ ጋር እንዲገደል ተመክሮበት ነበር፤ ነገር ግን አክስቱ የነበረችው በአባትዋ በኩል የንጉሥ አካዝያስ እኅት የሆነችው፥ የንጉሥ ኢዮራም ልጅ ይሆሼባዕ በመደበቅ ከሞት አዳነችው፤ እርሷም እርሱንና ሞግዚቱን ወስዳ በቤተ መቅደሱ ግቢ በሚገኘው ማረፊያ ክፍል ውስጥ ስለ ደበቀችው በዐታልያ እጅ ሳይገደል ቀረ።
ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ለመስጠት ስላደረገው ተስፋ፥ ጌታ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም።
በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፥ “በረከት በእርሷ ላይ አለና አታጥፉት” እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ አገልጋዮቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።