Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 23:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆች ከሆኑት ከይሮሐም ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከይሆሐናን ልጅ ከይስማኤል፣ ከዖቤድ ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከዓዳያ ልጅ ከማዕሤያ፣ ከዝክሪ ልጅ ከኤሊሳፋጥ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ካህኑ ዮዳሄ በሰባተኛው ዓመት የመቶ አለቆች ከነበሩት ከይሮሖም ልጅ ዐዛርያስ፥ ከይሆሐናን ልጅ እስማኤል፥ ከዖቤድ ልጅ ዐዛርያስ፥ ከዐዳያ ልጅ ማዕሴያና ከዚክሪ ልጅ ኤሊሻፋጥ ጋር ስምምነት ለማድረግ ብቃት ያለው መሆኑ ተሰማው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኢዮ​አዳ በረታ፤ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የኢ​ዮ​ራ​ምን ልጅ አዛ​ር​ያ​ስን፥ የኢ​ዮ​አ​ና​ንም ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን፥ የዖ​ቤ​ድ​ንም ልጅ አዛ​ር​ያን፥ የኢ​ዳ​ኢ​ንም ልጅ መዓ​ስ​ያን፥ የዘ​ካ​ር​ያ​ስ​ንም ልጅ ኤሊ​ሳ​ፋ​ጥን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 23:1
7 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።


በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ለመሻት ቃል ኪዳን አደረጉ፤


በእነርሱም ዘንድ ተሸሽጎ በጌታ ቤት ስድስት ዓመት ያህል ተቀመጠ፤ ጎቶልያም በምድሪቱ ላይ ነገሠች።


የይፅሃር ልጆች ቆራሕ፥ ኔፌግ፥ ዚክሪ ናቸው።


ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ኪዳን አደረገ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos