2 ዜና መዋዕል 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታንም ለመሻት ልቡን አላዘጋጀም ነበርና ክፉ ነገር አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ይሻ ዘንድ ልቡን ስላላዘጋጀ ክፉ ነገር አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ጥረት ባለማድረጉ ክፉ ነገር ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርንም ይሻ ዘንድ ልቡን አላቀናም ነበርና ክፉ ነገርን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ይሻ ዘንድ ልቡን አላዘጋጀም ነበርና ክፉ ነገር አደረገ። |
አቤቱ፥ የአባቶቻችን የአብርሃም፥ የይሰሐቅና የእስራኤል አምላክ ሆይ! ይህን አሳብ በሕዝብህ ልብ ለዘለዓለም ጠብቅ፥ ልባቸውንም ወደ አንተ አቅና።
ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለጌታ ለመሠዋት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ።
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በፍጹም ልባችሁ ወደ ጌታ የምትመለሱ ከሆነ፥ ባዕዳን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለጌታ አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።