1 ተሰሎንቄ 5:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካሙንም አጥብቃችሁ ያዙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ። |
ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወለደችኝም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእንናተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንደማይችል፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ ማፍራት አትችሉም።
እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና “ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን?” ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።
በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር የሰውን ነገር የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን ነገር ማንም አያውቅም።
እንዲህም ያለው እውቀት የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ እንድትወድዱ ስለሚረዳችሁ ነው፤ በዚህም ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ንጹሖችና ያለ ነቀፋ በመሆን
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ምስጉን የሆነውን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤
ከእነርሱም መካከል በየቤቱ እየተሽሎኮሎኩ በመግባት የኃጢአታቸው ሸክም የከበደባቸውንና በልዩ ልዩ ምኞትም ውስጥ የሚዋዠቁትን ደካማ ሴቶችን የሚያጠምዱ ይገኙባቸዋል።
ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መንፈሶች ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም መጥተዋልና።
“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንደማትችል፥ እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ‘ነን’ የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤
እንግዲህ ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንደምመጣብህ ከቶ አታውቅም።