1 ሳሙኤል 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ጋራ የሚጣሉ ይደቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል። “ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፥ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፥ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል። |
አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፤ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ፤
አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።
ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።
አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ ጌታ እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በጌታ ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ።”
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፥ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ጌታ ግን በዚያ ዕለት በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ አንጐዳጐደባቸው፤ እነርሱም እጅግ ተሸበሩ፤ በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመተውም ሸሹ።