Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 29:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለአንተ ደግሞ በመካከላቸው የተከፈተ አፍን እሰጥሃለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ አበቅላለሁ፤ በመካከላቸውም አፍህን እከፍታለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ይህ በሚሆንበት ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ አበረታለሁ፤ አንተም ሕዝቅኤል ሆይ! ሰዎች ሊያደምጡህ በሚችሉበት ቦታ ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ እንድትናገር አደርግሃለሁ፤ በዚህም ሁኔታ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “በዚያ ቀን ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቀን​ድን አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ንተ የተ​ከ​ፈተ አፍን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ በመካከላቸውም ለአንተ የተከፈተ አፍን እሰጣለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 29:21
21 Referencias Cruzadas  

በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፥ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።


በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።


የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ።


ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።


አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥ ዓመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና።


በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያቈጠቁጣል፥ ያብባልም፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።


“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


በዚያን ቀን አፍህ ላመለጠው ሰው ይከፈታል፥ ትናገራለህም፥ ከዚያ በኋላም ድዳ አትሆንም። ስለዚህ ምልክት ትሆናቸዋለህ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ከእንግዲህ ወዲያ ለእስራኤል ቤት መታመኛ አይሆንም፥ እነርሱን በተከተሉ ጊዜ በደልን ያሳስባል፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ለእስራኤል ቤት የመቃ በትር ሆነዋልና በግብጽ የሚኖሩ ሁሉ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


የግብጽ ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ምክንያቱም ወንዙ የእኔ ነው፥ የሠራሁትም እኔ ነኝ ብሏልና።


ምላስህን ከትናጋህ ጋር አጣብቃታለሁ፥ አንተም ዲዳ ትሆናለህ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና የሚገስጽ ሰው አትሆንባቸውም።


ነገር ግን በተናገርሁህ ጊዜ አፍህን እከፍታለሁ፥ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ የሚሰማ ይስማ፥ የማይሰማም አይስማ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።


በአገልጋዩ በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፥


ተቃዋሚዎቻችሁ በሙሉ ሊቃወሙትና ሊከራከሩት የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።


ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos