1 ነገሥት 8:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ፥ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዓይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ዕለት አንሥቶ፣ ስሜ በዚያ እንዲጠራና ቤተ መቅደስ እንዲሠራበት ከመላው የእስራኤል ነገድ አንድም ከተማ አልመረጥሁም፤ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲመራ ግን ዳዊትን መረጥሁት።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዐይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጬአለሁ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእርስዋም ቤት ይሠራልኝ ዘንድ፥ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማን አልመረጥሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ።” |
ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳም ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ።”
ነገር ግን የእስራኤል አምላክ ጌታ በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ እንዲሆን መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ሊያነግሠኝና ሊመርጠኝ ወደደ።
ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ ብትፈጽሟቸውም፥ ከእናንተ ውስጥ የሆኑ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜ እንዲኖርበት ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።”
ነገር ግን በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደነበረው ስፍራዬ ሂዱ፥ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ምን እንዳደረግሁበት እዩ።
ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።
ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።