Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ‘ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዐይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጬአለሁ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ዕለት አንሥቶ፣ ስሜ በዚያ እንዲጠራና ቤተ መቅደስ እንዲሠራበት ከመላው የእስራኤል ነገድ አንድም ከተማ አልመረጥሁም፤ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲመራ ግን ዳዊትን መረጥሁት።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ፥ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዓይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ።’

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእ​ር​ስ​ዋም ቤት ይሠ​ራ​ልኝ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 8:16
17 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ


ስሜ ይጠራበታል ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ።


ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳም ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ።”


ነገር ግን በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ናታንን እንዲህ አለው፤


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ይሁዳን በእስራኤል ላይ መሪ ነገድ አድርጎ መርጦታል፤ ከይሁዳም የእኔን ቤተሰብ፥ ከእኔም ቤተሰብ እኔን የእስራኤል ንጉሥ እንድሆን መረጠኝ፤ የእኔም ዘሮች ነገሥታት ሆነው እንደሚያስተዳድሩ ቃል ገብቶልኛል።


እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል፤ መኖሪያውም ሊያደርጋት ይፈልጋል።


ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ ከበጎች መሰማሪያም ወሰደው፤


አንተ አስቀድመህ፦ “ከመረጥኩት ሰው ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፤ ለአገልጋዬ ለዳዊት የተስፋ ቃል ሰጠሁት” ብለህ ነበር፤


እኔ እንድመለክበት በመጀመሪያ መርጬው ወደነበረው ቦታ ወደ ሴሎ ሂዱ፤ እዚያም ምን እንዳደረግሁት ተመልከቱ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ኃጢአት ምክንያት ሴሎን ደመሰስኩት።


ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።


አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤


እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ከንጉሥነት ስለ ሻርኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ድረስ ነው? እኔ እርሱ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ ይኖር ዘንድ አልፈልገውም። ይልቅስ የወይራ ዘይት በቀንድ ሞልተህ በመያዝ በቤተልሔም ወደሚኖረው እሴይ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ዘንድ ሂድ፤ እኔ ከእርሱ ልጆች መካከል አንዱን ንጉሥ እንዲሆን መርጬአለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos