1 ነገሥት 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪራም የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ ዙሪያው ዐሥራ ሁለት ክንድ የሆነ፣ ሁለት የናስ ምሰሶዎች ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤቱ ውስጥ ላለው ወለል ሁለቱን የናስ አዕማድ ሠራ፤ የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዓምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዓምድ እንዲሁ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱን የናስ አዕማድ አደረገ፤ የአንዱም ዐምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ የዐምዱም ውፍረት አንድ ጋት ነበረ፤ ውስጠ ክፍትም ነበረ። ሁለተኛውም ዐምድ እንዲሁ ነበረ። |
ሑራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምሰሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፤ ከቤተ መቅደሱ መግቢያ በር በስተ ደቡብ በኩል የቆመው ምሰሶ “ያኪን” ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሰሶ ደግሞ ቦዔዝ ተባለ።
ሁለቱ ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹም ላይ የነበሩትን ማቶቶች የሚመስሉ ጉልላቶች፥ በምሰሶውም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች የሚሸፍኑት ሁለቱ መረቦች።
ባቢሎናውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን የነሐስ ዐምዶች፥ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ከነሐስ የተሠራውን ታላቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሰባበሩ፤ ነሐሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
ከለዳውያንም በጌታ ቤት የነበሩትን የናስ ዓምዶች በጌታም ቤት የነበሩትን የውኃ ማመላለሻ ፉርጎዎችንና የናሱን ኩሬ ሰባበሩ፥ ናሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
እነዚህም ዓምዶች፥ የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የዙሪያውም ልኬት ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍረቱም አራት የጣት ስንዝር ያህል ነበረ፥ መሀል ለመሀልም ክፍት ነበረ።
የመተላለፊያው ርዝመት ሀያ ክንድ፥ ወርዱ ደግሞ ዐሥራ አንድ ክንድ ነበረ፤ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ደረጃዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን አንድ በዚያ ወገን ሆነው በመቃኖቹ አጠገብ የግንብ አዕማድ ነበሩ።