ሕዝቅኤል 40:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)49 የመተላለፊያው ርዝመት ሀያ ክንድ፥ ወርዱ ደግሞ ዐሥራ አንድ ክንድ ነበረ፤ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ደረጃዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን አንድ በዚያ ወገን ሆነው በመቃኖቹ አጠገብ የግንብ አዕማድ ነበሩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም49 የመተላለፊያው በረንዳ ርዝመት ሃያ ክንድ፣ ከፊት እስከ ኋላ ያለውም ወርድ ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበር። ወደ ቤተ መቅደሱም የሚያደርሱ ዐሥር ደረጃዎች የነበሩ ሲሆን፣ በየዐምዱም ጐንና ጐን ምሰሶዎች ነበሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም49 የመግቢያው ክፍል ርዝመት ኻያ ክንድ፥ ወርዱ ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበር፤ ዐሥር የመወጣጫ ደረጃዎቹም ወደዚያ ያደርሱ ነበር፤ በሁለቱ መወጣጫ ደረጃዎች ጐን ዐምዶች ነበሩ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)49 የደጀ ሰላሙም ርዝመት ሃያ ክንድ፥ ወርዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፥ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ዐሥር ደረጃዎች ነበሩ፤ አንድ በዚህ ወገን፥ አንድም በዚያ ወገን ሆነው በመቃኖቹ አጠገብ የግንብ አዕማድ ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)49 የደጀ ሰላሙም ርዝመት ሀያ ክንድ ወርዱም አሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፥ ወደ እርሱም የሚያደርሱ አሥር ደረጃዎች ነበሩ፥ አንድ በዚህ ወገን አንድም በዚያ ወገን ሆነው በመቃኖቹ አጠገብ የግንብ አዕማድ ነበሩ። Ver Capítulo |