ዮሴፍም፥ “ይህንንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባርያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው።
1 ነገሥት 21:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአዴር ልጅ እንዲህ ይላል፦ “ብርህና ወርቅህ ለእኔ ነው፥ ሴቶችህና መልካካሞቹም ልጆችህ ለእኔ ናቸው” ብሎ ወደ ከተማይቱ መልእክተኞችን ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡቴ ግን አክዓብን፣ “ዐፅመ ርስቴን እለቅቅልህ ዘንድ እግዚአብሔር አይበለው” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡቴም “ይህን የወይን ተክል ቦታ የወረስኩት ከቀድሞ አያቶቼ ነው፤ ለአንተ ከመስጠትስ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ!” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወልደ አዴር እንዲህ ይላል፦ ብርህና ወርቅህ የእኔ ነው፤ ሚስቶችህና ልጆችህም የእኔ ናቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወልደ አዴር እንዲህ ይላል፦ ብርህና ወርቅህ ለእኔ ነው፤ ሴቶችህና መልካካሞቹም ልጆችህ ለእኔ ናቸው ብሎ ወደ ከተማይቱ መልእክተኞችን ላከ። |
ዮሴፍም፥ “ይህንንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባርያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው።
እርሱም እንዲህ አለ፦ “ይህን እንዳደርግ አምላኬ አይፈቅድልኝም፤ በነፍሳቸው የደፈሩትን የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን? ነፍሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው አምጥተውታል።” ስለዚህም ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱም ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው።
ስለዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ የአባቶቹን ነገድ ርስት ይያዝ።
በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።
እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።
እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? በጭራሽ! ነገር ግን በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር፤ ሕጉ “አትመኝ” ባይል ኖሮ ምኞትን አላውቅም ነበር።
ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል እንደሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን የአካል ክፍሎች ወስጄ የአመንዝራ ክፍሎች አካል ላድርጋቸውን? ፈጽሞ ከቶ አይገባም።
በማደሪያው ፊት ለፊት ካለው ከአምላካችን ከጌታ መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በጌታ ላይ በማመፅ ጌታንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”
ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት ጌታን እንዳልበድል ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።