ሕዝቅኤል 46:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 መስፍኑ ሕዝቡን ከይዞታቸው ሊጨቁናቸው ርስታቸውን አይውሰድባቸው፤ ሕዝቤ ሁሉ ከይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆቹ ርስትን ይስጥ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ገዥው ከንብረታቸው በማፈናቀል፤ የትኛውንም የሕዝቡን ርስት መውሰድ አይገባውም፤ ለወንድ ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ንብረት ነው፤ ይኸውም ከሕዝቤ ማንም ከርስቱ እንዳይነቀል ነው።’ ” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 በሥልጣን ላይ ያለው መስፍን ርስት ከሕዝቡ ነጥቆ መውሰድ የለበትም፤ ለልጆቹ ከፍሎ የሚሰጠው መሬት ለራሱ ከተመደበለት ድርሻ ላይ ብቻ መሆን አለበት፤ በዚህም ዐይነት የርስት ድርሻቸውን በመቀማት ሕዝቤን አይጨቊን።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይወሰድ፤ ሕዝቤ ሁሉ ከየይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆቹ ርስትን ይስጥ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይውሰድ፥ ሕዝቤ ሁሉ ከይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆች ርስትን ይስጥ። Ver Capítulo |